Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ኢ/ክ/መ/ የጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-16-46-01-05
  • Website
  • Deadline06 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-06 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Construction Works , Sanitary Ware

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም በትምህርት እና በጤና ጽ/ቤት በተያዘ ካፒታል በጀት በወረዳው ውስጥ በተለያዩ ቀበሌዎች 1ኛ. በመላ ናሃ ት/ቤት፡- ሎት 1- ዘመናዊ የሴቶች መፀዳጃ እና ሎት 2- የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ፤ 2ኛ. በጋይሳ ት/ቤት:- ሎት 1- የጣርያ ውሃ ማሰባሰብ እና ሎት 2- የቆሻሻ ማቃጠያ፤

በደ/ኢ/ክ/መ/ የጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም በትምህርት እና በጤና ጽ/ቤት በተያዘ ካፒታል በጀት በወረዳው ውስጥ በተለያዩ ቀበሌዎች 1ኛ. በመላ ናሃ ት/ቤት፡- ሎት 1- ዘመናዊ የሴቶች መፀዳጃ እና ሎት 2- የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ፤ 2ኛ. በጋይሳ ት/ቤት:- ሎት 1- የጣርያ ውሃ ማሰባሰብ እና ሎት 2- የቆሻሻ ማቃጠያ፤ 3ኛ:- በደሌ ጤና ጣብያ የፈሳሽ እና ደረቅ ቆሻሻ ጉድጓድ፤ 4ኛ- በሻቻ ቀበሌ ጤና ኬላ ሽታ አልባ መፀዳጃ ቤት፤ 5ኛ፡- በሜላ ናሃ ማዘጋጃ ቀበሌ ሽድ ግንባታ ሥራ፤ 6ኛ፡- በገልጣ ማዘጋጃ ቀበሌ ጤና ኬላ ደረቅ ቆሻሻ ጉድጓድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በመንግሥት ዕቃና አገልግሎት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሥራ በጥሬ ገንዘብ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችሉ፤ ከላይ የተዘረዘሩ መረጃዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በአንድ እናት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዛላ ወረዳ ገቢ/ባለ/ሥ/ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡: ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በዕለቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በዕለቱ በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

•        ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በተባለው ቀንና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን ጭምር እንገልፃለን፡፡

•        የጨረታ ሠነዱ በግ/ን/ሥ/ሂደት ይገኛል፡፡

•        ከመሃንድስ ግመታ ከ20 ፐርሰንት በታች ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-13-07-46-50 ወይም 09-16-46-01-05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender