Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
  • Address ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 57 42
  • Websitehttps://aarevenuesbureau.gov.et/
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-31 00:00:00
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment , Electronics Materials , Camera

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር : 005/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

•        ሎት አንድ - ዲጅታል ካሜራ ከነ ሙሉ መለዋወጫ ጋር (with Accessary)፤

•        ሎት ሁለት - ለስብሰባ አዳራሽ የሚሆን ሞንታርቦ ሚክሰር ከነ ሙሉ መለዋወጫ ጋር (with Accessary)፤

በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2.     በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) በ4፡00 በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 205 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 2%፤ ለሎት ሁለት 2% የሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ C.O ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO መሰራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት።

5.     ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 11፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ /ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።

7.     ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።

8.     ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

9.     ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011 557 57 42 / 011 557 57 19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

Save Tender