Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ ስራ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት


የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ ስራ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህም

      ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ                     ሎት 4 ቋሚ አላቂ እቃዎች

      ሎት 2 ህትመት                                ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ

      ሎት 3 የጽዳት እቃዎች                        ሎት 6 ፈርኒቸር /የቢሮ መገልገያ እቃዎች

ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ በዘርፉ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች

1.     በዘመኑ የታደሰ ተዛማጅ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችል።

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው።

3.     የግዥ መጠን ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ከፋይ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል።

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1- 6 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን መረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ኮፒዎች ላይ በመጠቀም እና ኦርጅናሉን ለማመሳከር በእጅ በመያዝ ማቅረብ አለባቸው።

5.     የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ ወይ እስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች እያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት መግዛት ይቻላል።

7.     በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 3% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8.     በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ ከጨረታው ውድቅ ይሆናል። እንዲሁ በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ የበዛበት ከሆነ እና ፓራፍ ከላደረጉ እንዲሁም ጨረታ ሰነዱ በፍሉድ የተነካ ከጨረታው ውድቅ ይሆናል።

9.     ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትብት ሰዓት የሚያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገቢ ይሆናል።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሳተፍ ዋናና ኮፒውን በማያያዝ በጥንቃቄ ሁለት ፖስታ በማሸግ በወረዳው ፍ/ቤት ግዥና ንብረት ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በማስገባት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 14/5/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16 ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

•        ለተጫራቾች መረጃ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚሸጠውን የጨረታ መመሪያ መመልከት ይችላሉ። እንዲሁም የወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ንብረት ቡድን በግንባር በመቅረብ እንዲሁም ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 033 116 0084/12 ጥያቄያችሁን ማቅረብ ይችላሉ። ሳምፕል ለተቀመጠበት እቃ በወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማየት ይቻላል።

•        የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ ወደ ፊት ባለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን።

 

አድራሻችን፡- በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት

 

በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት

ወረኢሉ፤

Save Tender