Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት አመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት የስፖርት ትጥቅ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን፣የህክምና እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት አመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት የስፖርት ትጥቅ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን፣ የህክምና እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ሁኔታ ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው።

1.     በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት መቅረብ የሚችል።

2.     ተጫራቾች በተሰማሩበት የንግድ የዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ ንግድ ፍቃዱ ያለውና ዋናውን በማሳየት ኮፒን ማያያዝ አለበት።

3.     ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፍኬት) ያለውና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

2.     ተጫራቾች ባሸነፏቸው ኤሊክትሮኒክስ እቃዎች የሁለት አመት ዋስትና እና የተለያዩ የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ የማባዣ ቀለሞች ቶነሮች/ የአንድ አመት ዋስትና መስጠት አለባቸው።

3.     ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ አይነት ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሰንጠረዥ ዝርዝር መሰረት ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ማቅረብ አለባቸው። ሲፒኦ ያላቀረበ ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።

 

ተ.ቁ

ሎት (የእቃዎች ዝርዝር)

ሲፒኦ ማስያዣ ብር መጠን

 

ብር

ሣንቲም

1

ሎት 1 ደንብ ልብስ

7,091

40

2

ሎት2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

7,758

62

3

ሎት 3 የትምህርት ዕቃዎች

13,567

22

4

ሎት 4 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

11,760

00

5

ሎት 5 የህክምና ዕቃዎች

1,555

60

6

ሎት 6 ቋሚ ዕቃ

22,802

56

 

5.     ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው

6.      በሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ VAT 15% ተሰልቶ መካተት ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን VAT እንደተካተተበት ተደርጎ ይወሰዳል።

7.      ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አርጅናል ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ላይ ማህተም በማድረግ ከኮፒ ጋር በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

8.      የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል።

9.      መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. መ/ቤቱ የሚጫረተውን እቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20 በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።

11. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የጉልበት ወጪ በቁሙ ቅጥር ግቢ በሚገኘው ንብረት ክፍል ማድረስ አለባቸው።

12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011 1 26 62 73/ 011 1 58 57 06/

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሬስቶራንት ወረድ ብሎ የአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Save Tender