የከሚሴ መም/ት/ት ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽ/መሣሪያዎችን፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የትምህርት መረጃ (ዕቃዎችን)፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የመኪና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Kamise College of Teachers Education (የከሚሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የከሚሴ መም/ት/ት ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽ/መሣሪያዎችን፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የትምህርት መረጃ (ዕቃዎችን)፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የመኪና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በየ ዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1ኛ. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2ኛ. የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር/Tin/ ያላቸው፡፡
3ኛ. የግዢ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4ኛ. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁ.1 እስከ 3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጂናልና ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5ኛ. ከላይ የተጠቀሱትን የዕቃ አይነቶች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መግለጫ/specification/ብር 100/ አንድ መቶ/ ለእያንዳንዱ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ፡፡
6ኛ. የሚቀርቡት ዕቃዎች በሙሉ ኦርጂናልና ኮሌጁን ለሌላ ኪሳራ የማይዳርጉ መሆን አለባቸው፡፡
7ኛ. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 1% ቢድ ቦንድ በባንክበተረጋገጠ ሲፒአ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ኦርጂናል እና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው ይህ የጨረታ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ በኮሌጁ ግዢ ፋይ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 21 ማስገባት አለባቸው፡፡
9ኛ. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር በ21ኛው ቀን ማለትም በኮሌጁ ግዢ ፋይ/ ቢሮ ቁጥር 21 ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
10ኛ. የጨረታው አሽናፊዎች ማሸነፋቸው በደብዳቤ እንደተገለጸላቸው 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡
1ኛ. አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ኮሌጁ ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
12ኛ. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0960807878 ላይ በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
13ኛ. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የከሚሴ መም/ት/ት ኮሌጅ
