Tender Detail

Tender Details

  • Company የማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
  • Address ልደታ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline31 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-31 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎን ያስራውን ጂ+1 ህንፃ የምድር ቤቱን የተለያዩ ክፍሎች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

የማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት


የንግድ ቤት ጨረታ ማስታወቂያ

 

የማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎን ያስራውን ጂ+1 ህንፃ የምድር ቤቱን የተለያዩ ክፍሎች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች የሚሰሩት የንግድ /ቢዝነስ/ አይነት ከቤተክርስቲያኗ ሥርዓት አምልኮ እና ከኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ጋር በማይቃረን መልኩ ሆኖ በተለያዩ የንግድ አይነቶች መጫረትና መሥራት የሚችል ሲሆን (ለሁሉም የንግድ ቤቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር ብር 2000.00 ሆኖ)

1.     የንግድ ቤት ቁጥር 01 ..........................  16.36 ካሬ ሜትር

2.     የንግድ ቤት ቁጥር 02 ..........................  31.05 ካሬ ሜትር

3.     የንግድ ቤት ቁጥር 03 ..........................  31.53 ካሬ ሜትር

4.     የንግድ ቤት ቁጥር 05 ..........................  14.45 ካሬ ሜትር ሲሆኑ

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በደብሩ እስታስቲክስ ክፍል በሥራ ሰዓት ከ3-6 ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው የአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት እና የልደታ ቂርቆስ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቤተክህነት ተወካዮችና የሚመለከታቸው የደብሩ የሥራ ኃላፊዎች እና የሰበካ ጉባኤ አባላት እንዲሁም ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በ23/5/2018 ዓ.ም ከጧቱ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል። ለአሸናፊዎች በ5 ቀናት ውስጥ በማስታወቂያ ይገለፃል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

1.     የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 ከእለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ በመግዛት የሚከራዩበትን ዋጋ እና የንግድ ሥራ ዓይነቱን ሞልቶ ማቅረብ

2.     የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ (CPO) የጠቅላላ ዋጋውን 20% ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ ማስገባት

3.     የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባዔ አባልነት መታወቂያ ማቅረብ

4.     የቀበሌ መታወቂያ (ፋይዳ) እና የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል

5.     ደብሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናስታውቃለን።

 

የደብሩ አስ/ሰ/ጉ/ጽ/ቤት

 

Save Tender