በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም ጽ/መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የውሃ የግንባታ እቃዎች፣ ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ የውሃ ክሎሪን የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ፣ የማዳበሪያ ከረጢት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም ጽ/መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የውሃ የግንባታ እቃዎች፣ ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ የውሃ ክሎሪን የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ፣ የማዳበሪያ ከረጢት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. 1.ለ2018 ዓ.ም የታደሰና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
3. 3 የገዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም የማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ብር ለሚወዳደሩበት ሰነድ በመግዛት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የተጠየቁትን እቃዎች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ መሠረት መሙላት ያለባቸው ሲሆን : ሳንፕል ለቀረበላቸው እቃዎች መስ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሠረት ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ የጽ መሣሪያ ብር 40000.00፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 50000.00፣ የውሃ ግንባታ እቃዎች ብር 50000፣ ሲሚንቶ ብር 6000፣ አሸዋ ብር 5000.00፤ የውሃ ክሎሪን ብር 2000.00፣ የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ ብር 60000፣ ማዳበሪያ ከረጢት ብር 10000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በመሙላት በመፈረምና በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመ/ቤቱን አድራሻ፣ የድርጅቱን አድራሻ፣ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 |አራት ሰዓት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል። የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለው እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ነው።
9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ /በዓል/ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎት የሚያወዳድር ስለሆነ በአንድ ምድብ ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ሳይሞሉ መተው አይቻልም በሉት ያልሞላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
11. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
12. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀላቸው ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው።
13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 0443 መደወል ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
