Tender Detail

Tender Details

  • Company አብክመ ጤና ቢሮ
  • Address ባሕር ዳር፣የአማራ ክልል ፣ኢትዮጲያ, Phone: 058-222-1127
  • Website
  • Deadline29 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-29 00:00:00
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

አብክመ ጤና ቢሮ በክልል ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

አብክመ ጤና ቢሮ


ማስታወቂያ ጨረታና ጥሪ

አብክመ ጤና ቢሮ በክልል ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::

2. የግበር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት⁄ የሚያቀርቡ፡፡

3. ከላይ በተራ ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በባንክየተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላላ ዋጋ ከ500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር /መብለጥ የለበትም፡፡

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በጊዜያዊነት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

8. ለሕክምና መሳሪያ ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ አርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የቴከኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።

9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

10. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

 

11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ አብክመ ጤና ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት።

12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 አሥራ አምስት ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 1000.00 / አንድ ሺህ ብር/ በመከፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ባለሙያዎች እጅ በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል፡፡

13. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብከመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ

ባሕር ዳር

Save Tender