አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ለዋናው መ/ቤት ህንጻ የጥበቃና የጽዳት አገልግሎት ለጥበቃውና ለጽዳቱ አስፈላጊ ግብዓቶችን በሙሉ ተጫራቹ ችሎ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ የጥበቃና ጽዳት አገልግሎት ግዠ ቁጥር 04/2018
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ለዋናው መ/ቤት ህንጻ የጥበቃና የጽዳት አገልግሎት ለጥበቃውና ለጽዳቱ አስፈላጊ ግብዓቶችን በሙሉ ተጫራቹ ችሎ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸው የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ወቅታዊ የሆነ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ከሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ።
3. ተጫራቾች በዘርፉ አምስት አመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለውና የድርጅታቸውን አጠቃላይ ሁኔታ መግለጫ (company profile) ማቅረብ የሚችሉ የሚያቀርቧቸው የጥበቃ የጽዳት ባለሙያዎች የትምህርት ዝግጅት 8ኛ ክፍልና ከዚያ በላይ ያጠናቀቁ፣የጥበቃ
አገልግሎት ሙያ ወይም ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ሆኖ በጥሩ ስነምግባር የታነጹ እና ቢያንስ በሙያው 2 አመትና ከዚያ በላይ የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት ልምድ ያላቸው ሰራተኞችን ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች ለተሰማሩበት ድርጅት ለሚፈጠር አደጋ ሙሉ ኢንሹራንስ የገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ሲሰሩ ከቆዩበት ድርጅቶች ቢያንስ ከ3 መ/ቤት የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000(ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ቴከኒካል ና ፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻው በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ቴክኒካል ፖስታው ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 21/2018 ዓ.ም የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ጥር 21/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው በቀን 21/5/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
11. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድረሻ:- ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ
