በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ሁለተኛ ዙር ግልፅ የጨረታ/የእቃ ግዥ) ማስታወቂያ የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ብቻ ማቅረብ
ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ ብር
ሎት 1. የፅዳት እቃዎች ብር 7,070
ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 5,000
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር ዐ4 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ዐ4 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን በእለቱ 10፡00 ታሽጎ 10፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ህ/ሰብ ቅ/1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከቦሌ ድልድይ 400 ሜትር ገባ ብሎ ቦሌ ሆምስ ፊት ለፊት ስልክ፡- 011 8 21 77 36
በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
