የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ከዚህ በታች የተገለፀው መስፈርት ከሚያሟሉ ድርጅቶች ከ170 እስከ 200 ሠራተኞች የሚሆኑ የዩኒፎርም ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማስፋት ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ከዚህ በታች የተገለፀው መስፈርት ከሚያሟሉ ድርጅቶች ከ170 እስከ 200 ሠራተኞች የሚሆኑ የዩኒፎርም ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማስፋት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት -
1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው ሆነው የምስክር ወረቀቱ የተሠጣቸው እና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት በክበቡ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፤
3. የጨረታ ሰነዱን በመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ገንዘብ ያዥ ድረስ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት እስከ ምሽት 11፡00 ሠዓት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና አንድ ኮፒ በመያዝ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፤
4. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ መክፈቻ ቀን ለእያንዳንዱ ሠነድ 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፤
5. ይህ ጨረታ ባለቀ በ10ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ዩኒፎርሙን ሰፍተው በ1 ወር ውስጥ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
7. የጨረታ ሠነዱ ስርዝ ድልዝ ቢኖረው፣ ባይፈረም፣ በፍሉድ ቢጠፋ ከጨረታው ይሠረዛል፤
8. በተጠየቀው መስፈርት መሠረት ናሙና ጨርቅ ማቅረብ የሚችልና በናሙናው መሠረት ጥራቱን የጠበቀ ዩኒፎርም መስፋት የሚችል፤ የጨርቁ አይነት 6ሺ መሆን አለበት
9. ድርጅታችን በሚፈልገው ዲዛይን መሠረት ለመሠራት ፍቃደኛ የሆነ፤
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ
