Tender Detail

Tender Details

  • Company Fana Media Corporation (ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011551-67-77
  • Website
  • Deadline21 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-21 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Cloth And Shoes

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ ሎት-1 (የፅዳት እቃዎችና ስቴሽነሪ) እንዲሁም ሎት-2 (የሰራተኞች ደንብ ልብስ) ለመግዛት በድጋሜ ግልፅ ጨረታ በማውጣት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Fana Media Corporation (ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ ሎት-1 (የፅዳት እቃዎችና ስቴሽነሪ) እንዲሁም ሎት-2 (የሰራተኞች ደንብ ልብስ) ለመግዛት በድጋሜ ግልፅ ጨረታ በማውጣት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT/ የምዝገባ የምስከር ወረቀት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑ ግብርየተከፈለበትን ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. የጨረታው ውድድር በድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን ውል ሰጭ/ገዥ/ድርጅትን ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ድርጅት ሊመርጥ ይችላል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት በዋናው መ/ቤት በደንበኞች አገልግሎት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቶች ለሎት-2 የጨረታ ሰነዱን ቴከኒካል እና ፋናንሽል እንዲሁም ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት በተለያየ ፖስታ በማሸግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ 4፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

7. ለሎት-1 እንዲሁም ለሎት-2 አስፈላጊ ናሙናዎችና ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ መቅረብ ይኖርበታል።

8. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

9. ተጫራቾች ለሎት-1 ፡- 40,000/አርባ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት-2, 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/በባንከ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 011551-67-77

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ.

Save Tender