Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2026-01-26 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በኩል በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለመንግስት መ/ቤቶች የቢሮ ዕቃዎችና የጽህፈት /መሣሪያዎች /እስቴሽነሪ/ጥቅል ግዥ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በኩል በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለመንግስት መ/ቤቶች የቢሮ ዕቃዎችና የጽህፈት /መሣሪያዎች /እስቴሽነሪ/ጥቅል ግዥ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ያላችሁ፣
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የገበራችሁ፣
  3. የዘመኑን የንግድ ፍቃድ ያሳደሳችሁ፣
  4. ቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣
  5. ከዚህ በፊት በመንግስት ሥራ አፈጻጸም ላይ ምንም ዓይነት ክስ የሌላችሁ፣
  6. ዋጋው ከነቫት ማስገባት የሚችል፣
  7. መጫረቻ ሰነድ መግዛት የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አርቤጎና ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስ/ሥ/ሂደት ከቢሮ ቀጥር 12 መውሰድ የሚችል፤
  8. በጨረታ ሰነድ ላይ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልተው በእያንዳንዱ ዶክሜንት ላይ ህጋዊ ማህተም መመታት ይኖርበታል፤
  9. መጫረቻ ሠነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ የሚችል፤
  10. የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፈያ ማዘዣ /CPO/ እውቅና ባላቸው ባንኮች ብቻ ማቅረብ የሚችል፤
  11. ጨረታውን አሸናፊ የሆነ ድርጅት ላሸነፈበት ዕቃዎች ከመ/ቤቱ ጋር ውል መግባት የሚችል፤
  12. አሸናፊ ለሆነበት ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ የውል ዋስትና performance guar antee /10%/ አሥር በመቶ ማስያዝ የሚችል፣
  13. በራሱ ወጪ እስከ ቦታው አርቤጎና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ/ ድረስ ማቅረብ የሚችል
  14. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በ22ኛው ቀን የተዘጋጀው ህጋዊ የጨረታ ሣጥን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ሆኖ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ህጋዊ ተጫራች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አርቤጎና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ቢሮ ቁጥር 12 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ ተጫራች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም፤ የጨረታውን መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ ስለጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0916310368፣ 0916052461 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender