Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-11-48-00
  • Website
  • Deadline16 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityእያንዳንዱ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ እና ለህትመት 3,000 (ሶስት ሺህ ብር)
  • opening date2026-01-16 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/18

 

በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ በመንግስት ግዢ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና /orginal እና ቅጂ /copy/ ኤንቨሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት በቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል መግባት ይኖርበታል፡፡
  3. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩ እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በcpo ከዋናው (orginal) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ለህትመት ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በcpo ከዋናው (orginal) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት መስሪያ ቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20 /ሃያ በመቶ/ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  10. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የእቃ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ ያህል በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡- 0111114800

 

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender