በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት
የንግድ ቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
- የቤቱ አድራሻ፡- ፒያሳ ሁለገብ ሕንጻ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 151 h1ኛ እስከ 4ኛ ፎቅ የሆነውን የንግድ ማዕከል፣
- መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ፣
- ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውሃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል።
- ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፍልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለበት።
- ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፤ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፤ የሙያ አገልግሎት ስጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በጥቅልም ሆነ በተናጥል ሲወዳደሩ የሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5,000.00 በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ቤቱን ከፋፍሎ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ
ስ.ቁ. 0111-57-47-99
ወይም በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ።
