Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የቀራንዮ ጤና ጣቢያ
  • Address ከጦር ኃይሎች ወደ ቀራንዮ የሺ ደበሌ በሚወስደው መንገድ ወረዳ 08 ፅ/ቤት በስተጀርባ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-38-39-040
  • Website
  • Deadline19 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000.00
  • opening date2026-01-19 00:00:00
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የቀራንዮ ጤና ጣቢያ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት፣

ሎትı ቋሚ ዕቃዎች

በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ 20,000.00 ማስያዝ የሚችል።

  • የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒአ ማስያዝ የሚችል።
  • አንዱ በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  • ተጫራቹ ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን መሸጫ በየሎቱ ዋጋ ብር 300.00 ነው::
  • ቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉት በአመረታችሁት ዕቃ ብቻ ሲሆን አምራች መሆናችሁን የሚገልዕ ደብዳቤ ባደራጃችሁ ፅ/ቤት ሀላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኃል
  • ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 56 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • ተጫራች ድርጅቶች ያዘጋጀውን ሰፔስፍኬሽን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

ማሳሰቢያ፤

  • ጤና ጣቢያው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ጤና ጣቢያው ለጨረታ አሸናፊው ውል ከመዋዋሉ በፊት 20% ወደላይ መጨመር 20% ወደታች መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተወደዳሪዎች ለአሸናፊዎች ዕቃ በቀረበው ስፔስፍኬሽን መሠረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • የሚቀርቡትን እቃዎች በተቋሙ ጥራት ኮሚቴ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡

አድራሻ

ከጦር ኃይሎች ወደቀራንዮ የሺደበሌ በሚወስደው መንገድ ወረዳ 08 ፅ/ቤት በስተጀርባ ቀ/ጤ/ጣቢያ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-38-39-040

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀራንዮ ጤና ጣቢያ

Save Tender