በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጅማ ሪጅን ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጅማ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/SC&PGS/JB/NCB-003/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጅማ ሪጅን ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታው መዝጊያ ቀን |
የጨረታው መክፈቻ ቀን |
|
1 |
ያገለገሉ ጎማዎች 7.50/16 |
በቁጥር |
245 |
22,000.00 |
ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
|
2 |
ያገለገሉ ጎማዎች 12.00/22 |
በቁጥር |
80 |
|||
|
3 |
አሮጌ ቆርቆሮ |
በቁጥር |
640 |
|||
|
4 |
የነዳጅ ታንከር ባለ 4 15000 ሊትር በግምት |
በቁጥር |
1 |
|||
|
5 |
የትራንስፎርመር ዘይት በርሜል |
በቁጥር |
35 |
|||
|
6 |
አሮጌ የመኪና ባትሪ |
በቁጥር |
131 |
|||
|
7 |
ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣የድራም ብረቶች ትልቁና ትንሹ እንዲሁም አሮጌ የብረት ምሰሶዎች |
ኪ.ግ |
3000 |
1 ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EEU Jimma Region 1000156094157) የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ስዓት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕከምናና ግብርና ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን ሰፕላይ ቼን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
2 ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በጅማ ሪጅን እቃ ግምጃቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
3 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንከ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት ጅማ ሪጅን ሰፕላይ ቼን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡
5. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 047-2113757 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን
