የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 2/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1፡- የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች፣
- ሎት 2፡- የደንብ ልብስ
በዚሁ መሰረት ከላይ ለተጠቀሱ ዕቃዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፡-
- የታደሰ የዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት እና የዕቃ አቅራቢነት ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል፡፡
- ያልታገደ የንግድ ፍቃድ ወይም ታግዶ የነበረ ከሆነ የእገዳ ጊዜውን ስለመጨረሱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው 4ኛ ፎቅ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቢሮ ቁጥር 06 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን የሥራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጨረቱት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች 70,000 (ሰባ ሺህ ብር) እና ለደንብ ልብስ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በእራሳቸው ፈቃድ በጊዜው አለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች በውሉ መሰረት ግዥ የሚፈጸምባቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ አቅርበው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የመዘረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የመ/ቤቱ አድራሻ፡- በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ 1 ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን (SBC) ቢሮ ጀርባ ባለው የሲዳማ ክልል ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-212-71-38
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
