በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ቆረጣ ስራ የሚሆን የማሽን ኪራይ ለመከራየት፤ የመኪና ጎማ፤ የወተት ተዋጽኦ ፌሪቪኬሽን እና የስፖርት ትጥቅ ግዥ ለመግዛት ያስችል ዘንድ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች እና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
የአማራ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 04/18
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ቆረጣ ስራ የሚሆን የማሽን ኪራይ ለመከራየት፤ የመኪና ጎማ፤ የወተት ተዋጽኦ ፌሪቪኬሽን እና የስፖርት ትጥቅ ግዥ ለመግዛት ያስችል ዘንድ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች እና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TiN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የማሽን ኪራይ አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥ /ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የመኪና ጎማ፤ የወተት ተዋጽኦ ፌሪቪኬሽን እና የስፖርት ትጥቅ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የማሽን ኪራይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። 21ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ እንዲሁም የመኪና ጎማ፤ የወተት ተዋጽኦ ፌሪቪኬሽን እና የስፖርት ትጥቅ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የማሽን ኪራይ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጪ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0948 08 87 32 / 0973 80 72 93 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ከተማ አለፍ ብሎ እንገኛለን፡፡
የቡልጋ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት
ቱለፋ
