በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት አንድ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት ሁለት ፈርኒቸር፣ ሎት ሶስት የሞተር ጎማና ከመነዳሪ፣ ሎት አራት የውሃ እቃዎች፣ ሎት አምስት የደንብ ልብስ እና ሎት ስድስት ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0001
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት አንድ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት ሁለት ፈርኒቸር፣ ሎት ሶስት የሞተር ጎማና ከመነዳሪ፣ ሎት አራት የውሃ እቃዎች፣ ሎት አምስት የደንብ ልብስ እና ሎት ስድስት ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፣ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ Online /በኦንላየን/ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት አንድ እስከ ሎት አምስት እያንዳንዳቸው ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ) እና ለሎት ስድስት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ) በም/አ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በም/አ/ወ/ገቢዎች/ጽ/ቤት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ቅጂ ሰነዶችን በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ማስከበሪያው በኦርጂናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ አሸናፊው ዕቃዎቹን እስከ ቢሮአችን የሚያጓጉዝ ወጪ በራሱ ይሸፍናል፡፡
- ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀነ 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- የቫት ገንዘብ ክፍያ የምንፈጽመው የጠቅላላው የቫት ገንዘቡ 50% ብቻ ሲሆን ቀሪው 50% ደረሰኝ ቆርጠን በመስጠት እራሳችን የምንሰበስብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 0113430173/0113430614 ይደውሉ
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ሐዋሪያት
