Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline08 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየሚጫረቱበት የንግድ ሱቅ ከሚሰጠው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በማዕከሉ ግቢ የሚገኘውን የንግድ ቤት ለተጠቃሚዎች በግልፅ ጨረታ ማከራየት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በማዕከሉ ግቢ የሚገኘውን የንግድ ቤት ለተጠቃሚዎች በግልፅ ጨረታ ማከራየት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የንግድ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

ቁጥር

ካሬ ሜትር

1

በአስፓልቱ ዳር አድማ በታኝ ፊት ለፊት የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሬስቶራንት የነበረ

 

 

2

በመከላከያ ምህንድስና ፊት ለፊት ያለ

 

 

 

  1. ማዕከሉ ለኪራይ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አስተዳደርና ፋይናንስ ከፍል በመቅረብና የማይመለስ 100 ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች የተወዳደሩባቸውን የንግድ ቤቶች ዝርዝር ሁኔታ በዚሁ ሰነድ ተያይዞ በሚገኘው የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ቅፅ ሞልተው ተፈላጊ ሰነዶችን በማካተት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለከራዩ የመረጡትን ለአንድ ካሬ ሜትር የሚሰጡትን ዋጋ አባዝተው ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራች የሚጫረቱበት የንግድ ሱቅ ከሚሰጠው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የሚሆነውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋጋጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር ዋናውን በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ከሚሰጡት ጠቅላላ ዋጋ ከ10 በመቶ በታች የጨረታ ዋስትና ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  5. የንግድ ቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ተጫራቹ ለአንድ ካሬ ሜትር በሰጠው ዋጋ ተባዝቶ የሚገኘውን የገንዘብ መጠን ነው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳዳሩበት የንግድ ቤት ሞልቶ ከሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 1 ቅፅ ጋር የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የከፈሉበትን ደረሰኝ አብሮ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም፡፡
  8. የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ 1 ቅጽ በታሸገ ፖስታ ሆኖ እላዩ ላይ የተጫራቾች ሙሉ ሰም በመግለፅ መጥቀስ አለበት።
  9. የተወዳደረበት የንግድ ቤት አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነቱ በማዕከሉ የማስታወቂያ ቦርድ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ5 /አምስት /ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል ቀርቦ ውል መዋዋል ይኖርበታል።
  10. በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የኪራይ ውል ያልተዋዋለ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ዋስትና /cpo/ ለጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ገቢ ተደርጎ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ ሁለተኛ የወጣው ተጫራች ፈቃደኛ ከሆነ አንደኛ የወጣው አሸናፊ በሰጠው ዋጋ ሊከራይ ይችላል፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት ማግኘት ይቻላል፡፡
  12. የጨረታ ሰነድ አከፋፈትን በተመለከተ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃንሜዳ ስፖርትና ትምህርት ስልጠና ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  13. ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ከወር ክፍያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  14. ማእከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት በቢሮ የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል

Save Tender