የአፈጻጸም ከሳሽ ራቢያ ጃፋር እና በአፈጻጸም ተከሳሽ ሐጂ መንሱር መሃመድ እና ጣልቃ ገቢ ነኢማ ሙክታር መካከል ስላለው የአፈጻጸም ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 3 አለም ባንክ አካባቢ ስልጤ ሰፈር እንሻ መስጂድ አካባቢ በኮብል እስቶን መቶ ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ የመኖሪያ እና የንግድ ቤት የሚሸጥ ስለሆነ ለመግዛት የሚፈልግ ሰው በቦታው ተገኝቶ መግዛት የሚችል መሆኑን በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ያሳውቃል።
በነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የፍትሐብሔር ችሎት ቡድን
2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈጻጸም ከሳሽ ራቢያ ጃፋር እና በአፈጻጸም ተከሳሽ ሐጂ መንሱር መሃመድ እና ጣልቃ ገቢ ነኢማ ሙክታር መካከል ስላለው የአፈጻጸም ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 3 አለም ባንክ አካባቢ ስልጤ ሰፈር እንሻ መስጂድ አካባቢ በኮብል እስቶን መቶ ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ የመኖሪያ እና የንግድ ቤት አዋሳኝ በምስራቅ ተካ አሰፋ እና ብርሃኑ ደስታ በምዕራብ መሃመድ በሰሜን የመኪና መንገድ በደቡብ ከድር መሃመድ መካከል የሚገኝ ሆኖ የይዞታው ስፋት ሰባት መቶ ስልሳ ስድስት ካሬ ሜትር (766ሜ2) የሆነ በባለሙያ የቀረበውን ግምት የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 661,824.00 (ስድስት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሀያ አራት) በቀን 18/05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 አወዳድሮ አብላጫ ዋጋ ለሰጠው አካል የሚሸጥ ስለሆነ ለመግዛት የሚፈልግ ሰው በቦታው ተገኝቶ መግዛት የሚችል መሆኑን በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት እያሳወቀ ተጫራቾች በነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ስም ተመዝግበው በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1079807071216 በሆነው ገቢ በማድረግ ሲፒኦ ይዘው በጨረታው ቦታ ቀርበው እንዲወዳደሩ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- የሞባይል ስልክ ቁጥር 091805727 በመደወል ማጣራት ይቻላል፡፡
በነቀምቴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የፍትሐብሔር ችሎት ቡድን
