Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ አዲስ አበባ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ስ.ክ.ቢ.ግ.ጨ 004/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

ሎት 1የፅህፈት መሳሪያዎች (በድጋሚ የወጣ)

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች (በድጋሚ የወጣ)

ሎት 3የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ሙሉ ልብስ (በድጋሚ የወጣ)

ሎት 4 የስፖርት ትጥቅ

  • ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
  • ተጫራቾች በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ዌብሳይት ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ማስያዝ አለባቸው

ሎት 1 ብር 30,000/ሰላሳ ሺ ብር/

ሎት 2 ብር 10,000/አስር ሺ ብር/

ሎት 3 ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺ ብር/

ሎት 4 ብር 35,000.00 /ሰላሳ አምስት ሺ ብር/

  • ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ ሲገለጽለት ያሸነፈበትን 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በCPO ማስያዝ አለባቸው
  • ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 300 በመክፈል 5 ኪሎ ከሚገኘው ስፖርት ኮሚሽን ህንፃ 6ኛ ፎቅ ግዢና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ መውሰድ ይችላሉ፤
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወይም በሌሉበት በመ/ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤
  • ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።

አድራሻ፡- አምስት ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም ጀርባ የስፖርት ኮሚሽን ህንፃ 6ኛ ፎቅ ለበለጠመረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 8 124579

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ

አዲስ አበባ

Save Tender