Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ሰበታ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-3-38-13-83
  • Website
  • Deadline06 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security1% ብቻ
  • opening date2026-01-06 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment

በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ በ2018 ዓ.ም Lot 1 የደንብ ልብስ Lot 2 የፅዳት ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ በ2018 ዓ.ም Lot 1 የደንብ ልብስ Lot 2 የፅዳት ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. ዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችል።
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፕ ከኦርጅናል ፋይናንሻል ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  7. ዊዝ ሆልድ ታክስ /2%/ ለመቁረጥ ፈቃደኛ የሆነ።
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 1% ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫርቾች የጨረታ ሰነዱን በተናጠል ማቅረብ አለባቸው።
  10. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል 9 ቁጥር ገቢዎች ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ይከፈታል ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  12. ጨረታው የሚገመገመው በሚቀርበው የተናጠል ዋጋ ነው።
  13. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ድርጅታችን ድረስ ማቅረብ የሚችል።
  14. የጨረታ ሣጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  15. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113-38 13 83/ 0942 70 85 56

 

በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ

 

Save Tender