የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በቦንጋ ከተማ የሚገኘውን ህንፃ ለቢሮ እና ለመጋዘን አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት
በቦንጋ ከተማ የሚገኘውን የኮርፖሬሽን ህንፃ ለማከራየት
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ስ.ኮ/ብግጨ/2/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በቦንጋ ከተማ የሚገኘውን ህንፃ ለቢሮ እና ለመጋዘን አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
ህንፃው ብሮድባንድ ኢንተርኔት የተገጠመለትና ዋይፋይ የገባ፣ የውሃ አገልግሎት እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ከአስተማማኝ ጥበቃ ጋር ያለው በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የመንግሥትም ሆነ የግል ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርትፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁ 4 ወይም ቦንጋ ከተማ ቀበሌ ካይ ኬላ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሎጂ አጠገብ ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ በሲ.ፒ.አ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝይ ይጠበቅባቸዋል።
የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
ጨረታው ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ይከናወናል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
ስልክ፡ 011470-90-95/0114-423608-0114-421312
ስልክ ቁጥር 093 727 6513
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት
