Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክ/ከተማ የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የደንብ ልብስ ካኪ ፖሊስተር 6,000 የአገር ውስጥ፣ የስፖርት ቱታ እና ሸራ ጫማ የሴት፣ የሱፍ ካፖርት አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች፣ ፕሪንተር፣ኮምፒውተር፣ ቴሌቭዥን የውሃ ማጣሪያ ማሽን፣ ኤልሼፕ ጠረጴዛ የቢሮ እስታንዳር፣ የስብሰባ ጠረጴዛ፣ ጠረጴዛ፣ የመምህራን ሎከር፣ የብረት የኮት መስቀያ ኮት አንገር የእንጨት፣ ኋይት ቦርድ እና ተዛማጅ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል፡፡

የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክ/ከተማ የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የደንብ ልብስ ካኪ ፖሊስተር 6,000 የአገር ውስጥ፣ የስፖርት ቱታ እና ሸራ ጫማ የሴት፣ የሱፍ ካፖርት አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች፣ ፕሪንተር፣ ኮምፒውተር፣ ቴሌቭዥን የውሃ ማጣሪያ ማሽን፣ ኤልሼፕ ጠረጴዛ የቢሮ እስታንዳር፣ የስብሰባ ጠረጴዛ፣ ጠረጴዛ፣ የመምህራን ሎከር፣ የብረት የኮት መስቀያ ኮት አንገር የእንጨት፣ ኋይት ቦርድ እና ተዛማጅ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይገባቸዋል።

  1. በተሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /TIN-NO/ ያላቸው ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው፣ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት CPO (ሲፒኦ) ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በመስሪያ ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ ናሙና የማይቀርብባቸውን እቃዎች በከለር ፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ከናሙና ጋር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ዕቃዎቹን እስከ ት/ቤቱ ማድረስ አለበት፡፡
  6. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 (አስራ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ ተሟልቶ ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ ሲፒኦ በኦርጅናል ውስጥ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተገዛው የጨረታ ሠነድ ሙሉ በሙሉ በተጫራቾች ዋጋው ተሞልቶ በየገፁ ተፈርሞበት መግባት አለበት፡፡
  7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ወይም እሴት ጨምረው ለሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ፣ የዘገየ ሰነድ፣ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ፣ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ እና ቀነ ገደብ የሚያስቀምጥ ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. አሸናፊ ተጫራች 10% የውል ማስከበሪያ CPO (ሲፒኦ) በመስሪያ ቤቴ ስም ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- አራት ኪሎ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ወደም አዲስ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011 1 54 45 31/011 1 23 28 40 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender