አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ባለው በጀት የተማሪዎች ሱቅ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ተሳኮ/ተሱ/003/2018/2025
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ባለው በጀት የተማሪዎች ሱቅ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ከላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች ታሽጎ ማህተም ባለው ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል እንዲያቀርቡ ይጋብዛሉ፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥት ጨረታ አዋጅ በተገለጸው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት የተማሪዎች ሱቅ ኪራይ አገልግሎት ግዥ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች ሆኖ
- ከስራው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽና በማንኛውም የመንግስት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት ከገቢዎችና ጉምሩክ የተሰጠ ወቅታዊ ደብዳቤ (Tax clearance)
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒ
- የተፈረመ እና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በቁጥር 8 ‹‹ለ›› በተገለጸው አድራሻ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ። ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጣቸውን ደብዳቤ በማቅረብ በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 8«ለ›› በተገለጸው አድራሻ የተማሪዎች ሱቅ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ቁጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ወይም ከዚህ ቀን በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ መጠን፡- 7,200.00 (ሰባት ሺ ሁለት መቶ ብር) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ለሁለት ወር የሚያገለግል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 8‹‹ሐ›› በተገለጸው አድራሻ ጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ሀ/ ሰነዶቹ የወጣበት አድራሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1
ለ/ ጨረታው የሚቀርብበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር +251 111-22-36-15
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ
