Tender Detail

Tender Details


የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል በግልፅ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል በግልፅ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 1ኛ. አንደኛ ደረጃ የባለሞያ የስፖርት ትጥቅ፣ 2ኛ. ሁለተኛ ደረጃ የአሰልጣኝ ትጥቅ፣ 3ኛ. የደንብ ልብስ፣ 4ኛ ማሊያና ቁምጣ፣ 5ኛ. የእግር ኳስ፣ 6ኛ የስፖርት እቃዎች፣ 7ኛ. የሬስቶራንት የምግብና እሽግ መጠጥ፣ 8ኛ. ትኩስ መጠጥ፣ 9ኛ. ሶፍት የገላ ሳሙና የልብስ ሳሙና በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ ለመሳተፍ የሚትችሉ ተጫራቾች

  1. ለመጫረት የምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች በሥራ መስክ የዘመኑን ግብርለመከፈላችሁ ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በመንግሥት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል (TIN NO) ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. የንግድ ሥራ መስክ የሚገልፅ በጀርባው ኮፒ ተደርጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና ቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።
  5. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር ይፈለጋል። ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉና ከተዋወሉ በኋላ ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ በውሉ መሰረት በህግ ይጠየቃሉ።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
  8. የተጫራቾች ሙሉ ስም ፊርማ ማህተም ያረፈበት አድራሻ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር እና ስልክ ቁጥራቸውን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከማእከሉ አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ ቀርቦ የማይመለስ 100 ብር መግዛት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሳጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። የሥራ ቀን ካልሆነ ግን በማግስቱ በሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  11. ተጫራቾች ጨረታውን በሚከፈትበት እለት ድርጅቱን የሚገልፅ ህጋዊ መታወቂያ እና ውክልና የሚገልፅ ደብዳቤ በመያዝ ጨረታው ሲከፈት መከታተል ይቻላል።
  12. ተጫራቾች የገዙት የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም መረጃ /ዶክመንት/ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  14. አሸናፊዋች ክፍያ የሚከፈለው የተጠየቀው እቃ በተጠየቀውና በአሸነፈው መሰረት ሙሉ በሙሉ ወደ ንበረት ክፍል ገቢ ተደርጎ ሞዴል 19 ከተቆረጠ በኋላ ነው።
  15. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማሰገባት ይጠበቅበታል።
  16. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረጫ ዋጋ ሲፒዩ /CPO/ በብር 10,000 /አስር ሺህ /ብር ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  17. ከላይ ለተዘረዘሩት ለሁሉም ተጫራቾች ካሸነፉ በኋላ ዋስትና ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ/ በ CPO ከባንከ የተረጋገጠ ማቅረብ አለበት።
  18. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ሳንፕል ማቅረብ አለባቸው።
  19. የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ማስገባት አለባቸው፡፡
  20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል

 

Save Tender