በአራዳ ክፍለ ከተማ መሬትና አስ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት አስ/ቅ/ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡- አ/ክ/ከ/መ/ል/አስ/ቅ/ጽ/ቤት/የን/ግ/አስ/01/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ መሬትና አስ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 ደንብ ልብስ
- ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 4 ህትመት
- ሎት 5 የመኪና ማስዋቢያ
ስለሆነም በጨረታው ተሳትፋችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራች
- ተጫራጮች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው: የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፡ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ የመለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አራዳ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን 2ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነድ ከገዙ በኋላ እዛው 2ኛ ፎቅ ከግዥና ንብረት አሰተዳደር ቡድን ክፍል ሰዱን መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ የሚወዳደሩበትን ለእያንዳንዱ ሎት ወይም የበጀት ርዕስ በሲፒዮ
ሎት1. የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
ሎት2 ደንብ ልብስ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
ሎት3 የጽዳት ዕቃዎች ብር 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/
ሎት3 ህትመትና ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
ሎት 4 የመኪና ማስዋብ ሥራዎች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራጮች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኢንቨሎፕ ላይ በመጻፍና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመሬት ልማትና አስ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ ላለባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙናው ለማይቀርብባቸው የዕቃ ዓይነቶች በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የአገልግሎት ሥራዎችን በተመለከተ በድርጅቱ ጋር በመሄድ የሚታይ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ ድምር ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ለመገምግም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ መ/ቤቱ ባስቀመጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት መሆናቸውን ወይም በሚቀርበው ናሙና፣ ጥራት፣ ዋስትና፣ አነስተኛ ዋጋ አጠቃሎ ለሚያቀርብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- በየሎቱ የሚሳተፉ ተወዳደሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው።
አድራሻ
በአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አሰተዳደር ቅ/ጽ/ቤት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ ውስጥ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡- 011-1-72-92-02
በአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት አስ/ቅ/ጽ/ቤት
