Tender Detail

Tender Details

  • Company የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
  • Address ደሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0331117670
  • Website
  • Deadline03 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2026-01-03 00:00:00
  • Categories Electronics Materials , Vehicle tire , Construction Works , Contractors

የአብክመ ጤና ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የኤሌክትሪክ እቃዎች ከእነኢንስታሌሽን ሥራ የመኪና ጎማ ግዥ፣ ከደረጃ 4 እና በታች የሆኑ ተቋራጭ የህንፃ እድሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአብክመ ጤና ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የኤሌክትሪክ እቃዎች ከእነኢንስታሌሽን ሥራ የመኪና ጎማ ግዥ፣ ከደረጃ 4 እና በታች የሆኑ ተቋራጭ የህንፃ እድሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም አግባብነት ያለቸውን ሁሉ በጨረታው እየጋበዝን

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦትና የአገልግሎት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን-ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
  4. የግዥው ወይም የአገልግሎቱ መጠን ከ200,000.00 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
  5. የህንፃ እድሳት ሥራ ለመሳተፍ ደረጃ 4 እና በታች የሆኑ ተቋራጭ መሆን አለበት
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቃል
  7. ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ብቻ ከአርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ይኖርባቸዋል የጨረታ በሚያስገቡበት ጊዜ ዋናው የጨረታ ሰነድ እና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ በማሸግ እንደገና ሁለቱንም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ በጥንቃቄ በስም በማሸግ የድርጅቱ ስም አድራሻውና ማህተም በመምተታ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣበት 15 ተከታታይ ቀናት በመጨረሻ በ16ኛ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ሆስፒታሉ ቫት (7.5) እና ዊዝ ሆልድ (3%) ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን፤
  12. ሆስፒታሉ በሚጋብዘው የቴከኒክ ባለሙያ ተረጋግጦ እቃው /አገልግሎቱ/ ገቢ ይሆናል፡፡
  13. ሆስፒታሉ በሚያቀርበው ናሙና እቃው ገቢ ይሆናል፡፡
  14. አስፈላጊ መረጃ መስጠት ከፈለጉ በሆስፒታሉ ስልክ ቁጥር 0331117670 መደወል ይችላሉ፡፡

 

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender