በአራዳ ክ/ከተማ የብሔራዊ ቤተ መንግሥት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሔራዊ ቤተ መንግሥት የመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ የብሔራዊ ቤተ መንግሥት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ብር 7500፣ ሎት 3 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ብር 6000፣ ሎት 4 የጽሕፈት መሣሪያዎች ብር 5200፣ ሎት 5 የትምህርት ዕቃዎች ብር 4000፣ ሎት 6 የተለያዩ የህትመት ሥራዎች ብር 8000 ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች ብር 7500፣ ሎት 8 የትራንስፖርት አገልግሎት ብር 12000 እና ሎት 9 የጭነት አገልግሎት ብር 7800 በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል።
በጨረታ መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፊኬት )ያለውና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ አይነት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ VAT 15% ተሰልቶ መካተት ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን VAT እንደተካተተበት ተደርጎ ይወሰዳል።፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ላይ ማህተም በማድረግ ከ1 ኮፒ ጋር በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ መ/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የፎቶ ናሙናዎችን በፖስታ በማሸግ እና ማህተብ በማድረግ ከጨረታ ሰነድ ውጪ ለብቻው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የሚጫረተውን ዕቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የጉልበት ወጪ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- የተሰረዘ እና የተደለዘ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 011 812 0130/ 011 111 8394/ 011 170 5050 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ናዝሬት ት/ቤት ወረድ ብሎ
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሔራዊ ቤተ መንግሥት
የመ/ደ/ት/ቤት
