በኢፌዴሪ መንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎት የሚሆን የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ከሚችሉ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ አስተዳደር
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢፌዴሪ መንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎት የሚሆን የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ከሚችሉ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ደሴ ከተማ ከመናፈሻ ከፍለ ከተማ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ያሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50/ አምሳ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ፖስታውን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 2፡30 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ በማስቆረጥ ከኦሪጅናል የዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስ/ቁ 033 312 5729
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ አስተዳደር
