የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ ጂ+10 ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply and fix Wooden Door ግዥ ለመፈፀም ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/ SF/188/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ ጂ+10 ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply and fix Wooden Door ግዥ ለመፈፀም ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
Supply and fix Wooden Door |
ለጃንሜዳ ጂ+10 ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/SF/188/2025 |
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት |
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት |
200,000.00 |
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ Info@adce-et.com
የድረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
