Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕር ዳር
  • Address ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ዉስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0582263095
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/
  • opening dateጨረታው በዚሁ ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  • Categories Wood And Wood Working , Forest And Tree Sales

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደሴ ዙሪያ፣ ተሁለደሬ፣ ጉና በጌምድር፣ ላይ ጋይንት፣ ወገራና ፋግታ ወረዳዎች የሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ደኖችንና የፌ/ጽድ ጣውላዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕር ዳር


የፌ/ጽድ ጣውላ እና ቁም ደን ሽያጬ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ደብረ ማርቆስ ከተማ የራባ የመንግስት ደን ውስጥ 473.046 ሜ/ኩብ የፌ/ጽድ ጣውላ፣ በምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ወረዳ ቀረር የመንግስት ደን ውስጥ 2973.32 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን ፣ በደ/ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ እና ተሁለደሬ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች በተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 9382.35 ሜ/ኩብ የፌ/ጽድ፣5.5 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ ቁም ደን እና የወደቀና የደረቀ የፌ/ጽድ 322.98 ሜ/ኩብ በድምሩ 9710.81 ሜ/ኩብ፣ ደ/ጎንደር ዞን ጉና በጌምድር፣ ላ/ጋይንት ወረዳ እና ማ/ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 4047.7 ሜ/ኩብ የፌ/ፅድና 24,962.85 ሜ/ኩብ ነጭ ባህር ዛፍ በድምሩ 29,010.35 ሜ/ኩብ ቁም ደን እና ደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ ላይ የሚገኝ 87.14 ሜ/ኩብ የፌ/ጽድ ጣውላ ፣ በአዊ ዞን ፋግታ ወረዳ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ 7110.54 ሜ/ኩብ የፈረንጅ ፅድና እንጅባራ ከተማ እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ 119.01 ሜ/ኩብ የፌ/ጽድ ጣውላ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች:-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ መሆን ይኖርባቸዋል::
  2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  3. ለጨረታ የቀረበውን ቁም ደን /ምርቶች/ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ ::
  4. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond} በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል.::
  6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን /ምርቶች/ በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የፌ/ጽድ ጣውላና የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ» ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 12/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን 23/2/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል::
  7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም:: ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል::
  8. ተጫራቾች ቁም ደኑን ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ከፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል::
  9. ተጫራቾች የጣውላ ምርት በተመለከተ በሎት የተቀመጠውን ሁሉንም ዋጋ መሙላት እና መግዛት አለባቸው
  10. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ::
  11. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095፣ ደ/ታቦር 0584410306፣ ደ/ብርሃን 0116375017፣ እንጅባራ 0582270485፣ ደ/ማርቆስ 0588719004 ፣ኮምቦልቻ 0914716636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል::

ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Amhara Forest Enterprise invites bids for the sale of government forest timber and logs, including softwood and hardwood, from various forests across Debre Markos, Finote Selam, Dessie, Tehuledere, Guna Begemder, Lay Gayint, Wegera and Fagita districts. Bidders need a renewed business licence and tax registration.
Save Tender