Tender Detail

Tender Details


ለደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል ለ2018ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1 ኬሚካል፣ ሎት2 ላብራቶሪ እቃዎች፣ ሎት3 አላቂ የቢሮ እቃዎች (የጽሕፈት መሣሪያ)፣ ሎት4 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት6 ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት7 የውሃ እና ኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት8 ኮምፒውተርና ተጓዳኝ እቃዎች፣ ሎት9 ቋሚ እቃዎች (ፈርኒቸር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

ለደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል ለ2018ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1 ኬሚካል፣ ሎት2 ላብራቶሪ እቃዎች፣ ሎት3 አላቂ የቢሮ እቃዎች (የጽሕፈት መሣሪያ)፣ ሎት4 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት6 ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት7 የውሃ እና ኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት8 ኮምፒውተርና ተጓዳኝ እቃዎች፣ ሎት9 ቋሚ እቃዎች (ፈርኒቸር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  3. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ / ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ኦሪጂናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ሊፈተሸ ይችላል።
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፤
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ማግኘት ይቻላል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በማእከሉ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከአሪጂናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
  11. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ የሚያስዝ ይሆናል፡፡
  12. ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ በሎት ድምር ነው።
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  14. ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ ቢሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ማእከሉ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0946206131/0914051398 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል

 

Save Tender