Tender Detail

Tender Details

  • Company F.D.R.E Authority for civil Society Organization (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን)
  • Address ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ኅብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-10-20-47-68
  • Websitehttps://acso.gov.et
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%)
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Generators , Materials , Electronics Materials , Vehicle , Kitchen Materials

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጀቶች ባለሥልጣን ከተዘጉ ድርጅቶች እና ለፈንድ ድጋፍ ካደረጉ ድርጅቶች ላይ ያገኛቸውን ንብረቶች እነሱም ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፣ ጄኔሬተር፣ ሶፋ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ኦቭን፣ ፍሪጅ እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

F.D.R.E Authority for civil Society Organization (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጀቶች ባለሥልጣን ከተዘጉ ድርጅቶች እና ለፈንድ ድጋፍ ካደረጉ ድርጅቶች ላይ ያገኛቸውን ንብረቶች እነሱም ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፣ ጄኔሬተር፣ ሶፋ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ኦቭን፣ ፍሪጅ እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከተቋሙ ግዢና ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በሚል ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ሲመጡ ተመላሽ ይሆናል፤ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት በጨረታ አፅዳቂ መፅደቁ ወይም ውድቅ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 የሥራ ቀናቶች ሆኖ በ11ኛው ቀን ጨረታው 4፡30 ተዘግቶ 5፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ከድርጅቱ የግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ ክፍል ቢሮ ቁጥር 605 የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 300 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ በመግዛት ከሰነዱ ላይ ሙሉ ዝርዝሩን ያገኛሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ኅብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 በመገኘት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች የሚገኙበት ቦታ ድሬዳዋ ወረዳ 09 ፖሊስ መሬት፣ ወረዳ 03 ካዚራ፣ ወረዳ 02 ሳቢያን አካባቢ፣ አፋር ክልል ሊጊያ ከተማ ጎይቶም ጋራጅ ፊት ለፊት እና ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ አለፍ ብሎ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በስተቀኝ በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ኒያላ ኢንሹራንስ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ፊት ለፊት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ተቋሙ በተከራየው መጋዘን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9:30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-558-24-37 / 09-01-19-09-39/09-13-95-20-41/011-558-24-02

 

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን

 

Save Tender