አዲስ ህይወት ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2018 ዓ.ም የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
አዲስ ህይወት ቅ/አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
አዲስ ህይወት ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2018 ዓ.ም
- የደንብ ልብስ ሎት 1 /አንድ/ በኢትዮጵያ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ፤
- የጽሕፈት መሳሪያ ሎት 2 /ሁለት/ በኢትዮጵያ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ፤
- የጽዳት እቃዎች ሎት 3 /ሦስት/በኢትዮጵያ 7000 /ሰባት ሺህ/ብር የጨረታ ማስከበሪያ፤
- የሕትመት እና የሕክምና እቃዎች ሎት 4/አራት/ በኢትዮጵያ 6000 /ስድስት ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ፤
- የቋሚ እቃዎች ሎት 5 /አምስት/ በኢትዮጵያ 16,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ፤
- የኤሌክትሮኒክስ/ ለማሽነሪ ጥገና ሎት 6 /ስድስት/ በኢትዮጵያ 2700 ሁለት ሺህ ሰባት መቶ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ፤
- የተለያዩ መሳሪያዎች ሎት 7/ሰባት/ በኢትዮጵያ 3900 /ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ፤
- ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ በአደራጁ ተቋም በሃላፊው የተፈረመ ወቅታዊ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ እና አምራች ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ በባለሙያ ሆነ በስራ ሂደት የተጻፈ ደብዳቤ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፤
- የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀበት ቋንቋ በአማርኛ ነው፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ እና ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለእያንዳንዱ ሎት በኢትዮጵያ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በግልጽ በመሙላት በጨረታ ሰነዱ ላይ ስም፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ቀን ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ቀናት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው/በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ በ4፡30
- በትምህርት ቤቱ ግዥ ቢሮ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ለሚጫረቱበት ሎት የጨረታውን ማስከበርያ CPO/በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ በአደራጁ ተቋም በኃላፊ የተጻፈ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፤
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረት ማቅረብ ካልቻሉ የአደራጁ ተቋም ኃላፊ ማለትም ደብዳቤውን የጻፈው አካል ሃላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል፤
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከር ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበርያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለምትጫረቱበት ሎት ቀድመው ናሙና ማምጣት ይኖርባቸዋል ናሙናውን ይዞ ለመምጣት አስቸጋሪ ለሆኑ እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ይጠበቃል። ካላመጡ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ።
- የጨረታው ሳጥን ከታሸገና ሰነዶችን መክፈት ከተጀመረ በኋላ ለሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
- 20% መጨመርም መቀነስም እንደምንችል እናሳውቃለን።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ሂደት አፈጻጸም ላይ ቅሬታ ካላቸው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7/ሰባት/ ቀናት ውስጥ ቅሬታዎችን የማቅረብ መብት አላቸው።
- ዊዞልድ ታክስ 3% ት/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ይቆረጣል፤
- ተጫራቾች ተወዳድረው ላሸነፉበት እቃ የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛም ሆነ የማውረጃ ወጪን መቻል ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት ተከታታይ ከ7/ሳበት ቀናት በኋላ በሶስተኛው /3/ቀን በወቅቱ ቀርበው ውል ካልተዋዋሉ የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል። በተጨማሪም ወደ ሁለተኛ ተጫራች የምንሄድ መሆኑን እናሳስባለን። እንዲሁም ውል ሲዋዋሉ ያሸነፍበት የእቃ 10% (አስር ፐርሰንት ባሸነፉበት ዕቃ መጠን የውል ማስከበርያ CPO በመሰዝ በተጨማሪም እቃውን በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት የመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ባይሆን ጨረታውን ለቀጣይ አስተላልፈን ኃላፊነት የምንወስድ መሆኑን እናሳስባለን።
- ጥገና ተወዳዳሪዎች ጥገናውን ስትወዳደሩ ከነሙሉ እቃው እና የእጅ ዋጋ ጨምሮ ነው።
አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ ከ ከተማ በወረዳ 05 ከዘነበወርቅ ከፍ ብሎ ወደ ታቦት ማደርያ በሚወስደው መንገድ ኮልፌ ኢንዱስትሪያል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 369 7620/ 011 369 6945
አዲስ ህይወት ቅ/አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
