የመስከረም ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ሎት 1 የደንብ ልብስ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3 አላቂ የህክምና እቃዎች ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 5 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ሎት 6 የህንፃ ቁሳቁሶች ሎት 7 የደንብ ልብስ ስፌት አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 መስከረም ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 2/2018 ዓ.ም
የመስከረም ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ሎት 1 የደንብ ልብስ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3 አላቂ የህክምና እቃዎች ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 5 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ሎት 6 የህንፃ ቁሳቁሶች ሎት 7 የደንብ ልብስ ስፌት አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ለመወዳደር ይችላሉ።
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት በእያንዳንዱ ሎት (CPO) 5000 (አምስት ሺ ብር ብቻ ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ዕቃዎችን እስከ ት/ቤቱ ድረስ ማድረስ አለበት።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ይከፈታል።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ ዕቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ በፖስታ ታሽጎ በፋይናንስ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 557 9371 እና 011 557 1602 በመደወል እንዲሁም በአካል ግቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ በአታ ጤና ጣቢያ አጠገብ በመምጣት ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 መስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
*ግቢ ገብርኤል ጀርባ ባአታ ጤና ጣቢያ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011 557 9371 እና 011 557 1602
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 መስከረም ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት
