Tender Detail

Tender Details


የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ 2018 በጀት ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል።

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ


 

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ 2018 በጀት ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል፣ የዚህም ጨረታ የገንዘብ ምንጭ የመንግሥት ግምጃ ቤት እና የውስጥ ገቢ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ተጫራቾች

  • ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ

ስለመሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከአደራጃችሁ ተቋም የአምራችነት ደብዳቤ በማምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 411 የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ ሰነዱ ዉስጥ በሚገኝ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር መሰረት ከነቫቱ ሞልተው ያስገባሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ የፅህፈት እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1,000.00 ብር
  • ሎት 2 ቋሚ እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1,500.00 ብር
  • ሎት 3 የተለያዩ የህትመት ሥራዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 3,000.00 ብር
  • ሎት 4 የተለያዩ የጥገና ሥራዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 3,000 ብር
  • ሎት 5 የደንብ ልብሶች 800.00 ብር
  • ሎት 6 የፅዳት እቃዎች 500.00 ብር
  • ሎት 7 የተለያዩ ለጥገና ሥራ ላይ የሚውሉ እቃዎች 600.00 ብር
  • ሎት 8 የሰው የህክምና መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች 20,200 ብር

ተጫራቾች ያሸነፉበትን የዉል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በጤና ጣቢያው ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል ተጫራቾች ሙሉ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች የሚሞሉትን ክፍሎች ተሞልተው ሰነዱ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደረጎበት ይመለሳል፤ ለጥቃቅን ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ ከአደራጃችሁ ተቋም ማምጣት ይኖርባችሁዋል። ሙሉ ሰነዱ ላይ ፈርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች ተሞልተው ኮፒ ተደረጎ ከኮፒው ጋር ሲፒኦ ማሲያዝና መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ ተጫራቾች ሰነዳቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ጠዋቱ 2፡30 ተዘግቶ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጤና ጣቢያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል በማንኛውም ምከንያት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ወድቅ ይሆናል። መ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጥብቅ ማሳሰብያ፡- የህክምና መገልገያ መሳርያዎች ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ ሞልታችሁ የምታስገቡት የመድሃኒት ዋጋ ከሞላችሁበት ጋር ሳይሆን የህክምና እቃዎችን የሞላችሁበትን ፖስታውን ከተቋሙ የምትወስዱትን የጥራት መገለጫ (እስፔሲፊኬሽን) እና ሰለማሽኑ የሚገልፅ ካታሎማ አንድ ላይ በማድረግ ለብቻው ማስገባት ይኖርባችኋል።

አድራሻ፡- ከኮካ አደባባይ ወደ መሣለሚያ ወይም ከመሣለሚያ ወደ ኮካ አደባባይ በሚሄደው ዋና መንገድ ሲሄዱ የቀድሞ 24 ቀበሌ መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት ባለው ዳገታማ መንገድ 200 ሜትር እንደሄዱ በሚታየው ባለ አራት ፎቅ ህንፃ ላይ ያገኙናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0118-27-56-08 ወይም 0118-27-90-60/

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተጫራች እስፔስፊኬሽን /የጥራት ልዩ መግለጫ/ ከተገለፀላቸው ዕቃዎች ውጪ ለተወዳደሩበት ማንኛውም ዕቃዎች ናሙና እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ሳይከፈት ተመላሽ ይደረጋል ማለትም ለውድድር አይቀርብም። የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ሁሉ ከቫት ጋራ የተሰላ/ተጨማሪ እሴት ታክስን ያከተተ መሆን ይኖርበታል ከቫት ጋራ ያልተሰላ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያላከተተ ከሆነ ለአሠራራችን አመቺ ስለማይሆን ለውድድር አናቀርበውም፡፡

 

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ

 

Save Tender