በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን በኩታበር ወረዳ የኩታበር ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኩታበር ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን በኩታበር ወረዳ የኩታበር ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ማለትም፡-
- ሎት 1 :- የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ፡- የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3 ፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 4 :- የህንጻ መሳሪያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንጋብዛለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ በተጠቀሱት የንግድ ዘርፎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN number/ ያላቸው
- የሚሞሉት ዋጋ ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥ ተሳትፈው ያሸነፉትን እቃ ሳያቀርብ ቀርቶ በጨረታ እዳይሳተፍ ያልታገደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱት የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ኦርጂናል መረጃቸውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መገለጫዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ
- የጨረታ ሰነዶች በኩታበር ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጂ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል
- ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ሞልተው ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ላቀረቡት ዋጋ 3% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በፖስታ በማሸግ ኦርጂናል ዶክመንቱን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም የተጫራቹ ፊርማ መቀመጥ አለበት
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይና በፖስታው ላይ የተሟላ አድራሻቸውንና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል
- ጨረታውን ሆን ብሎ ለማዛባትና ለማጭበርበር የሞከረ ከጨረታ ውጭ የሚሆን መሆኑ
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት ቀናት (ቅዳሜን እና እሁድን ጨምሮ) ውስጥ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስራ ቡድን ክፍል ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የኩታበር ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
