Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወሎ ዞን የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወሎ ዞን የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡

  • ሎት-1. የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት-2 የፅዳት እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው አላቂ እቃዎች
  • ሎት 3 ፈርኒቸር
  • ሎት-4 ህትመት
  • ሎት-5. ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት-6 መድሀኒትና የህክምና መሳሪያዎች
  • ሎት-7. የመኪና እስፔር ፓርት መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት-8. ለሆስፒታሉ እድሳትና ጥገና፤ የማቴሪያል አቅርቦትና፤ የእጅ ዋጋ

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN ያላቸው፣
  4. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውንም ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሁሉንም እቃዎች ዝርዝር መግለጫ/ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሆስፒታሉ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ከሆነ የውል ማስከበሪያ 10% የሚያስይዝ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ባሸነፈው መሰረት ውል ባይወስድ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ስለዚህ ለጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሁሉንም የስራ ዘርፎች የጨረታውን ሰነድ በመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብቻ/ ከፍሎ መውሰድ ይችላል፡፡
  11. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በኤንቨሎፕ ላይ ስማቸውንና ስልክ ቁጥር በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  12. በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 71 በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ይከፈታል፡፡
  13. ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
  14. ጨረታው በሎት ስለሆነ አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ድምር መሰረት ነው አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃዎች በሆስፒታሉ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  15. በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሆስፒታሉ ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0963606473 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወሎ ዞን የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

Save Tender