በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለዲላ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለዲላ ቅ/ጽ/ቤት
የቤት ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 07/2018
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለዲላ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- የሚከራየው ቤት ሙሉ ግቢ ሆኖ ለመዝገብ ቤት የሚሆን አንድ ሰፋ ያለ ክፍል (ስፋቱ ቢያንስ 6×4 ሜትር) ያላነሱና ሌሎች ተጨማሪ 10 ያህል ለቢሮ አመቺ የሆኑ ስፋታቸው ቢያንስ ከ3×4 ያላነሱ ክፍሎች ያሉት መሆን ይኖርበታል።
- የኪራዩ ጊዜ ከየካቲት 01 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሶስት አመት የሚቆይ ይሆናል።
- የክፍያው ሁኔታ በሁለታችን ስምምነት መሠረት በየ 6 ወሩ ወይም በአመት አንድ ጊዜ በቅድሚያ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።
- ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ከሆኑ የማስረጃው ኮፒ አብሮ መቅረብ ያለበት ሲሆን፣ የሚሰጡትም ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልጽ ማመልከት አለባቸው፤ ካልተገለጸ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል።
- ቤቱ ህጋዊና የመንግስት ግብር እየተከፈለበት ያለ ስለመሆኑ ማስረጃ ያለውና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫው ኮፒ ሆኖ አብሮ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በዲላ ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመግዛት የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል፣ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ውጤት በሪጅን ጽ/ቤት (ሀዋሳ) በኩል ተከፍቶና ተወስኖ የሚገለጽ ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሪጅን ጽ/ቤት (ሀዋሳ) ስልክ ቁጥር 0462214317 ወይም 0462214140 ዲላ ቅ/ጽ/ቤት ሰን ሻይን ሰፈር፣ መልሂቅ ክሊኒክ ፊት ለፊት፣
ስልክ ቁጥር፡- 0463311007/0461311245
በመ/ሠ/ማ/ዋ/አስተዳደር የደቡብ ሪጅን
