በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለከተማው የውሃ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች /pipe fitting/ የቧንቧ ጥርስ ማውጫና መፍቻ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የሠራተኛ የጽዳት መገልገያ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለከተማው የውሃ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች /pipe fitting/ የቧንቧ ጥርስ ማውጫና መፍቻ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የሠራተኛ የጽዳት መገልገያ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ መወዳደር የምትፈልጉ፡-
- በዘርፉ የተመዘገበና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚህ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መረጃ ኮፒ ከፖስታው ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% እና ከዚያ በላይ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸውና ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፤
- ተጫራቾች በጨረታ መከፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታ መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል /የተጫረተው ባለቤት/ ወይም ሕጋዊ ውክልና ያለው አካል ኦርጂናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሱት ሎቾች ሠነድ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በእያንዳንዱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፤
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወያያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ወይም /የጨረታ ዶክሜንት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግና በመፈረም ሳይቀንሱ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፤
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ በነጠላ ሆኖ ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ አሸናፊ ስለሚሆን እያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት ባሉት ቀናት ውስጥ ውለታ በመግባት እቃዎቹን ኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ ማስረከብ ይኖርባችኋል፤
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0336610092/0910845646/0913442257 መደወል ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
