የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ. የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ. የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ፡-
Lot: 1 የስራ ላይ አደጋ መከላከያ አልባሳት (safety device) - NCB/ OACFLTD/AMF/10/2018
Lot: 2. የተለያዩ የስራ ላይ ደንብ ልብስ (uniform) ፡NCB/OACFLTD/ AMF/11/2018
Lot: 3 የንጽህና መጠበቂያ እና የፅዳት ዕቃዎች (Sundry) ፡ -NCB/OACELTD/ AMF/12/2018
Lot: 4: የፅህፈት መሳሪያዎች (Stationery) ፡-NCB/OACELTD/ AMF/13/2018
ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TINያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ) ።
ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት በኃላ 7፡00-10፡00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ-ቁሉምሳ ከሚገኘው ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ. የተ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለLOT 1 ብር 20.000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለLOT:2 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ፣ ለLOT:3 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ.ህ ብር) እና ለLOT 4 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለየብቻ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን LOT1 እና LOT:2 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ LOT:3 እና LOT:4 ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 6፡00 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ. የተ ሰባተኛ ፎቆ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 09 65 65 04 81/ 09 65 65 02 85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ. የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
