በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል።
ሎት 1 እና ሎት 3 የደንብ ልብስ ግዥና ስፌት እንዲሁም የስፖርት ዕቃዎች.......የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00
ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች………. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,500.00
ሎት 4 የፅዳት ዕቃዎ…………………. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,500.00
ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች………. የጨረታ ማሰከበሪያ ብር 12,500.00
ሎት 6 የቤተሙከራ ኬሚካሎች…. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
ሎት 7 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች……የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00
ሎት 8 የትራንስፖርት አገልግሎት…. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000
ሎት 9 የጥገና ሥራዎች…. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000
ሎት 10 የካፌ አገልግሎት…የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20000
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈለ - ናሙና (ሳምፕል) ለሚፈለግባቸው ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ የሚያቀርብ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ 10% (ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በፅህፈት ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የካቲት 23 አጠቃላይሁ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ በ3፡00 /ሶስት/ ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 /ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የገዛችሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ። ሙሉ ሰነዱን ያላስገባ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
- የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ተጫራቾች በመንግስት ግዥ ዌብሳይት ላይ ድርጅታችሁ ተመዝግቦ መገኘት አለበት።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112768120/0112303241/0112303054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አውቶብስ ተራ ወደመሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
