በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የመ/ሰላም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አጠቃላይ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ከሕጋዊ አቅራቢ የንግድ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራ ስልጠና ቢሮ የመካነ ሰላም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የመ/ሰላም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አጠቃላይ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማለትም፡-
1. ቋሚ የቢሮ እቃዎች 2. አላቂ የትምህርት እቃዎች
3. አላቂ የጽዳት እቃዎች 4. አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
5. የተለያዩ የኢንስታሌሽን እቃዎች 6. የተለያዩ የሠራተኛ ደንብ ልብሶችን
7. የተለያዩ የህትመት ሥራዎች እና 8. ሌሎች አላቂ እቃዎችን
ከሕጋዊ አቅራቢ የንግድ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች-
- በዘመኑ የታደስ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው።
- ጠቅላላ የግዥው መጠን ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚዝዙ እቃዎችን ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኪሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከታህሳስ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከመ/ሰላም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢ/ቁ 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የግዥ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መካነ-ሰላም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር - 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ሰላም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ እና ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ሰላም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 220 01 79 ላይ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የመ/ሰላም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
