ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላሉት የሕክምና ማዕከሎቹ አገልግሎት የሚውል አቡጀዲ የመኝታ ጨርቅ /DRAW SHEET/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Hamlin Fistula Ethiopia (ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ)
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
በድጋሚ የወጣ አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ክነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፣ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላሉት የሕክምና ማዕከሎቹ አገልግሎት የሚውል አቡጀዲ የመኝታ ጨርቅ /DRAW SHEET/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር የአማርኛው ዕትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /07/ ተከታታይ የሥራ ቀናት አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በመገኘት፣ ግዢው የሚፈፀምበትን የጨርቅ ናሙና በመመልከት እና ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጨረታው ተወዳዳሪ ድርጅቶች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማክስኞ ታህሳስ 07፣2018ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡00 በድርጅቱ የስብሰባ ማዕከል ይከፈታል።
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። ተጫራች ድርጅቶች ለሚኖራቸው ማናቸውም ጥያቄዎች ቀጥሎ በተመለከቱት የስልክ መስመሮች በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡-
ስልክ ቁጥር +251-113716544/45/46-የውስጥ መስመር 139/182
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
