የቤ/ጉ/ህ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን ኤሌክትሮኒክስና ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ህ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን ኤሌክትሮኒክስና ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች፡-
- በተሰማሩበት የስራ መስክ ሂጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የገንዘብ ሚኒስተር/የክልል ገ/ኢ/ል/ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና የውል ስምምነቱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ከስኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት በቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን የግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት ያለባቸው በመ/ቤታችን በተዘጋጀው በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፤ የጨረታ ሰነዱ ላይም የድርጅቱን ማህተም ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በፖስታ /በኢቨሎፕ/ በማሸግ ማስታወቂያው ከታተመበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በተቋሙ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መስገባት አለባቸው፤ ለሚወዳደሩትና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሂጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ፍላጎት ባይገኙ የጨረታው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት አይስተጓጎልም።
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተጣጣመ እና ቢያንስ እስከ ሁለት ወራት የሚፀና መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 2% ማስያዝ አለባቸው፣
- የጨረታው የመክፈቻ ቀናት በበዓላት/እሁድ/ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመዘረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
- ሆኖም ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም።
- ለበለጠ መረጃ በቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለሥልጣን የግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ/በስልክ ቁጥር 0572758718/0991287799/0930418789 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ።
የቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን
