Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ወደ ጀሞ በሚያስኬደው መንገድ ከአንበሳ ጋራዥ አለፍ ብሎ በናሰው ሪሊስቴት በአዲሱ መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113698159
  • Website
  • Deadline22 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለሎት 01 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 02 10,000.00 /አስር ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 03 8,000.00 /ስምንት ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 04 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/፣ ለሎት 5 10,000 /አስር ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 6 20,000 /ሃያ ሺ ብር ብቻ/
  • opening date2025-12-23 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Equipment And Accessories , Stationery Materials , Educational And Training Equipment And Machinery

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በቀን 22/12/2017ዓ/ም በግዥ መለያ ቁጥር 001/2018 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በገፅ 23 የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ታውቋል። ስለሆነም ተቋሙ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ጨረታው የተሰረዘ ሲሆን በድጋሚ በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ማለትም በየሎታቸው የተቀመጡ ሎት01 የደንብ ልብሶች፣ ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 03 አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 04 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 05 ሌሎች መሳሪያዎች፣ ሎት 06 ቋሚ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 02 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 /ስምንት ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 04 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/፣ ለሎት05 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 06 የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ለአላቂም ለቋሚም ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማለትም ለቋሚ እቃዎች በት\ቤቱ ፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ እየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በክ/ሂ/ግ/ን/አስ እና ጠ/አገ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በት/ቤቱ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ለእያንዳንዱ እቃዎች ቫት አካቶ ያለውን ዋጋ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች አምራችነታችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል።
  8. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11 ሰዓት ድረስ ውሎ ይዘጋ እና በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ እና ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  9. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም። በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

አድራሻ፡-

ን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ በወረዳ 13 ፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ ጀሞ

በሚያስኬደው መንገድ ከአንበሳ ጋራዥ አለፍ ብሎ በናሰው ሪሊስቴት

በአዲሱ መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ፡- 0113698159/0118961899

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender