የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/04/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ የውጭ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/04/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የአቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።
|
የአገልግሎት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ለተለየዩ አስራ ሁለት (12) ሪጅኖች የክሬን ኪራይ አገልግሎት ግዥ |
ለአንድ ሪጅን ሰላሳ ሺህ (30,000) ብር |
ታህሣስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ታህሣስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡01 ሰዓት |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 58 17 25 /011-5 5819 16 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
